ABC TV Live
ውድ የዐማራ ሕዝብ እና የዐማራ ሕዝብ ወዳጆች፤ እንዲሁም ሰብአዊነት፣ እኩልነት፣ ፍትኅ፣ ዲሞክራሲና በሰላም አብሮ መኖር ለሚያሳስባችሁ ሁሉ፤ የዐማራ መረጃ ማሰራጫ ማዕከል (ዐመማ) (Amhara Broadcasting Center (ABC)) በተሰኘ ስም የተመሠረተ ተቋም ስናስተዋውቃችሁ በከፍተኛ የደስታና የኃላፊነት ስሜት ነው።
የዐማራ መረጃ ማሰራጫ ማዕከል፤ ከደጋፊዎቹ በሚያገኘው የገንዘብ መዋጮ፤ የሳተላይት ቴሌቪዥን በመከራየት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ስርጭት የሚጀምር ሲሆን፣ በተጨማሪም በዐማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጉዳይ ላይ ለሚሠሩ የሚድያ ተቋማት ከክፍያ ነጻ የአየር ሰዐት ለመስጠት የተቋቋመ ነው።
የዐማራ መረጃ ማሰራጫ ማዕከል ነጻና ገለልተኛ ተቋም ሲሆን፤ አስተዳደሩም ለዐማራ ሕዝብ በሚቆረቆሩ ዐማራዎች በተዋቀረ ጠቅላላ ጉባዔ እና በጉባዔው በሚሰየም ቦርድ የሚመራ፤ እንዲሁም ሙሉ ተጠያቂነትና ግልጽነት ያለው አሠራር የሚከተል ነው።
ከዚህም ጋር በተያያዘ፤ በዐማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ የሚዘጋጁ እና በዐማራ ሕዝብ ጉዳይ የሚዘግቡና የሚተነትኑ ዝግጅቶችን የሚያቀርቡ ቡድኖችንና ተቋማትን ለማግኘትና ለመወያየት ጥረቶች እየተካሄዱ ሲሆን፤ ወደፊት በነዚህ ቋንቋዎች ዝግጅቶች ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸውን ሁሉ በመገናኛ ገጻችን ላይ በተቀመጠው አድራሻችን እንዲያገኙን እንጋብዛለን። በዐመማ ሳተላይት የሚሰራጩ ወይም ሊሰራጩ የታቀዱ ዝግጅቶች በወቅታዊ ሁኔታ ዘገባዎችና ትንታኔዎች፣ በታሪክ፣ በፖለቲካ፣ በምጣኔ ሀብት፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በባህል፣ በስነቋንቋ፣ በሳይንስ፣ በኑሮ ዘዴ፣ እንዲሁም በሌሎች ለዐማራ ሕዝብና ለአጋሮቹ ጠቃሚ አርዕስት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ABC TV via Satellite
Platform: Yahsat 52° East
Frequency: 12149 MHz
Symbol rate: 27500
Polarization: Vertical
Video Standard: DVB-S2
FEC: 3/4
ABC TV on TikTok
ABC TV on WhatsApp (click or scan)
Subscribe here, to support ABC TV
የሥራ ማስታወቂያ
በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው እና ወደሳተላይት ስርጭት የገባው ABC TV በሚከተሉት የሥራ ዘርፎች ብቁ ሙያተኞችን ለመቅጠር ይፈልጋል።
1) ሲኒየር የፕሮግራም አዘጋጅ
– በቴቪ ዝግጅቶች ላይ በተለይም ቃለመጠይቅ የማድረግ እና የዜና ዘገባ ልምድ ያለው ያላት፤
– የABC TV ኤዲቶሪያል መመሪያ ጠብቆ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፤
– በአማራው ሕዝብ የትግል ጉዳዮች እምነት ያለው/ያላት፤
– ከኢትዮጵያ ውጭ በአፍሪካ አገራት ፣ በአውሮፓ፣ አሜሪካ ወይም ካናዳ የሚኖር/የምትኖር፤
2) ሲኒየር የቪዲዮ እና ግራፊክስ ኤዲተር፤
– በቴቪ ፕሮዳክሽን ኤዲቲንግ ሥራ እና ቴክኒካል ሥራዎች ልምድ ያለው ያላት፤
– የABC TV ኤዲቶሪያል መመሪያ ጠብቆ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፤
– በአማራው ሕዝብ የትግል ጉዳዮች እምነት ያለው/ያላት፤
– ከኢትዮጵያ ውጭ በአፍሪካ አገራት ፣ በአውሮፓ፣ አሜሪካ ወይም ካናዳ የሚኖር/የምትኖር፤
ከላይ በተጠቀሱት የሥራ መስኮች ልምዱና ፍላጎቱ ያላችሁ ሙያተኞች ልምዳችሁንና ፍላጎታችሁን የሚገልፅ ማመልከቻ በኢሜል አድራሻችን info@amharabroadcasting.com መላክ ትችላላችሁ ።
ABV TV !